We humbly ask you to follow the spiritual services we release by subscribing to Milkya Media. Milkia Media - Milkia Media is a platform where integrated lessons, Mezmur, Advice, current church information, spiritual reactions, and the conspiracy of spirits are presented for teaching. If you are looking for anything related to Orthodox Tewahdo, you should make Milkia Media your first destination. Thank you for being family. ሚልክያ ሚዲያ ሰብስክራይብ በማድረግ የምንለቃቸውን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲከታተሉ በትህትና እንጠይቃለን። Milkia Media - ሚልክያ ሚዲያ የተዋህዶ ትምህርቶች፣ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ መንፈሳዊ ሪአክሽኖች ፣ የመናፍስት ሴራ በማወቅ ለማስተማርያነት የሚቀርቡበት መድረክ ነው። ማንኛውንም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የተመለከተ ቁም ነገር ሲፈልጉ የመጀመሪያ መድረሻዎን Milkia Media - ሚልክያ ሚዲያ ቢያደርጉ ይጠቀማሉ። ቤተሰብ ሰለሆኑ እናመስግናለን፡፡
የመዝሙር የስብከት እና መንፈሳዊ የሆኑ ቪድዩዎችን ሪያክሽን መስራት
የመዝሙር የስብከት እና መንፈሳዊ የሆኑ ቪድዩዎችን ሪያክሽን መስራት
ምዕመናን በተለያዩ ቋንቋዎች በዝማሬ በስብከት ተደራሻ ለማረግ ከልብ እንዲሰሩ እና ሙሉ ወጪያቸውን መሸፈን
ጥሩ ጥሩ ስብከቶችን ደግሞ አገልጋዮቹን በመጋበዝ እንዲሰብኩት ማድረግና መማሪያ ቪዲዪችን መስራት
መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ ሰ/ት/ቤት ላይ ማዘጋጀት እና ቪዲዪ መስራት
ጉባኤ በየቤተ ክርስቲያን ማዘጋጀት ጉባኤውን ማዘጋጀት፣ ጉባኤውን ጥሩ ዲኮር በመስራት እና ጉባዬው እንዲተላለፍ ማድረግ
ተሰጦ ያላቸው የስንበት ት/ቤት አገልጋዮችን ለአገልግሎት ተተኪ ሆነው እንዲሰሩ እና ሙሉ ወጪያቸውን መሸፈን
በጥያቄና መልስ ጥሩ ጥሩ ቪዲዮዎችን ማዘጋጀት ለምሳሌ “የሚልክያ ለእስራኤል ያለውን መልዕክት ሲያጠኑ ለሕይወቶ ምን ዓይነት መልዕክትን ያገኛሉ?” እና የሚልክያ የጠቀሳቸው ቃላት እንዴት ነው ከዘመናችን ጋር የሚዛመዱት?
“ኦርቶ ዶክስ” ፡- ማለት፤ ቃሉ የግሪክ ሲሆን፤ “ቀጥተኛ መንገድ (እውነተኛ ሃይማኖት)” ማለት ነው።
ቀጥተኛዋ መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ
ለነብሳቹሁም እረፍት ታገኛላቹሁ፡፡[ኤር 6÷16]
ነብዩ ኤርምያስ እንዳለው እዚህ ላይ እንግዲህ ቀጥተኛ
ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ሲሆን መንገድ ማለት ደግሞ
ሃይማኖት ማለት ነው፡፡
✔ ኢየሱስም ክርስቶስም አለ እኔ መንገድ እውነት
ሕይወት ነኝ ብልዋል፡፡[ዮሐ 14÷6]
ይህ ማለቱም የሃይማኖት መሰረታ ቹሁ እኔ ነኝ ማለቱ
ነው፡፡
✔ ኦርቶዶክስ ነው ሃይማኖቴ ስንል => ቀጥተኛ ናት
ሃይማኖታችን እያልን ነው፡፡
ተዋህዶ ማለት ተዋሃደ ከሚለው የግእዝ ግስ
የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሆነ መለኮትና ስጋ አንድ
ሆነ ማለት ነው፡፡ ከሁለት አካል አንድ አካል ፤ከሁለት
ባህርይ አንድ ባህርይ ሆነ ማለት ነው በሌላ አካሄድ ደግሞ
ተዋሃደ ማለት መለኮት ስጋ ለበሰ ከድንግል ማርያም
ከስጋዋ ስጋ ከነብሷ ነብስ ነሳ ማለታችን ነው፡፡
✔ ይህም ደግሞ ግልፅ የሆነ እውነት ነው፡፡
በጀመርያ ቃል ነበረ ፤ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ፤ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፡፡[ዮሐ 1÷1]
ቃልም ስጋ ሆነ፤ፀጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡[ዮሐ1÷14]
ስለዚህ ተዋህዶ ስንል ቃል ስጋ ለበሰ ማለታችን ነው፡፡
=>የተዋህዶ ልጆች ነን ስንልም የክርስቶስ ልጆች ነን
እያልን ነው፡፡
ክርስትያን ማለት ከክርስቶስ ስም የተወሰደ ሲሆን
ክርስቶስ ተከታዮች፤አማኞች ማለት ነው፡፡
ክርስቶስ አምላክ ነው፤ጌታ ነው፤ፈጣሪ ነው፤ፈራጅ ነው
ብለን የምናምን ክርስትያን ተብለን እንጠራለን፡፡
የክርስቶስ ሐዋርያትም በአንጾክያ ምክንያት ክርስቲያን
ተባሉ፡፡[ሐዋ 11÷26]
✔ በትዕቢት ተነፍቶ በዲያብሎስ ፍርድ
እንዳይወድቅ፤ሰው ሁሉ አዲስ ክርስቲያን አይሁን፡፡
[1ኛ ጢሞ 3÷16]
ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም
እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፡፡
[1ኛ ጴጥ 4÷16]
=>ክርስቲያን ነን ስንልም ክርስቶስን የምናመልክ
የምናምን ክርስቲያን ነን፡፡
ማለታችን ነው፡፡
ሃይማኖት መሠረት ነው፡፡ ምግባር ደግሞ ግድግዳና ጣሪያ ነው፡፡ እነዚህን የተዋሕዶ ምሳሌዎች ፍጹም የሚገልጹ አይደሉም ጥቂት ለመረዳት ያህል ነው እንጂ
ሚልክያ የሚለው ስያሜ “የኔ መልዕክተኛ” ማለት ነው (የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “ሚልክያ”)።
“ሚልክያስ” ማለት “መልአክ፣ ሐዋርያ፣ መልእክተኛ” ማለት ነው፡፡ ጥር ፰ ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንደሚያስረዳው ነቢዩ ሚልክያስ የተወለደው ሕዝቡ ከፄዋዌ (ከምርኮ) ከተመለሱ በኋላ ነው፡፡ ከሕፃንነቱ አንሥቶም የእግዚአብሔርን መንገድ የሚወድ ነበር፡፡ ሕዝቡም ይኽን አካኼዱን አይተው እጅግ ያከብሩት ነበር፡፡ ይኽን መልካምነቱንም አይተው “ከእግዚአብሔር የተላከ ነው” ሲሉ ስሙን ሚልክያስ ብለው ጠሩት፡፡
ልዑል እግዚአብሔር የቅዱሳንን አማላጅነት ይወድዳል፡፡ “ፃድቅ ስለኃጥአን ቤት ያስባል” ምሳ21÷12 ለእግዚአብሔር ባለቸው ቅርበት በጸሎት ና በቃል ኪዳን ያማልዳሉ ዘፍ20÷1-18 ት.ዳን12÷3 ት.ኤርም42÷2 የሀገሬ ሰውም “ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁም ቅርጫፉን መመልመል ግንዱን ለመቁረጥ ነው”ይላሉ፡፡
ዘጸ 25÷22፤ ዘኁ 7÷8-9 ዘጸ 24÷12 ዘጸ 31÷18 ፤ የዩዳኖስን ወንዝ ተከፍሏል፡፡፡ መ.ኢያሱ 3÷14-17 አስቸጋሪ የነበረው የያሪኮ ግንብ ፈርሷል፡፡መ.ኢያሱ 6÷1 የአሕዛብ ጣዓታት ተሰባብረዋል፡፡ 1ኛ ሳሙ 5÷1-12 እግዚአብሔርን ታቦት መዳፈር እንደማይገባን 1ኛ ሳሙ 4÷1-18 “ የዔሊ ልጆችን ማንሳት ይቻላል፡፡ ዖዛ የአሚናዳብ ልጅ እጁን በመላክ ታቦቱን ቢነካ ዕድሜው አጠረ እንጂ ብዙ አልቆየም 2ኛ ሳሙ6÷6-9
ምስጋና 2ኛሳሙ6÷16-23 ራቅ ብሎ መቆም መ.ኢያሱ 3÷3-4 ስግደት መ.ኢያሱ 7÷6 ዘጸ 33÷10 ታቦት ለምን በዛ? መልሱ ት.ሚልክ 1÷11 በኦሪትም አንድ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ብቻ ነበረች ታቦቱ በአንድ ብቻ ይወሰን ከአሉ ነብዩስ ለምን አንድ ብቻ አልሆነም ? ውሉደ ይሁዳዎች በአንድ ታቦት የማያምኑ ሁነው ሳለ ለምን በዛ ይላሉ? በዛ ብቻ ከማለት ቤተ መቅደሱ ለምን አንደ ብቻ ሆነ የሚለውን እንዴት ዘነጉት
2ኛ ቆሮ 6÷16 ራእይ 11÷1 “በሰማይ ታየ ማለቱ የታቦቱን ክብር ልዕልና ያሳየናል፡፡ ታቦት በቅዱሳን ስም እንደሚቀረጽ ት.ኢሳ 56÷4 ዘፍ 9 ÷20 “ በኖኀ የሳቀበት ካም ሲሆን ከነዓንን ስለምን ረገመው ? በመጀመሪያ የኖኀን ራቁት መሆኑን አይቶ የነገረው ከነዓን ነውና በዚህ ምክንያት ነው፡፡
መዝ108÷24 “ ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ ቅቤ በማጣትም ከሳ……… ት.ዳን.10÷3 “ሥጋና ጠጅ በአፌ አልገባም ሦሰት ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም” የጾም ወራትም አለ ?አዎ፡፡የሐዋ.27÷9
ሚልክያ ሚዲያ ሰብስክራይብ በማድረግ የምንለቃቸውን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲከታተሉ በትህትና እንጠይቃለን።
አድራሻ
አዲስ አበባ, ኢትዮጰያ
E-mail አድራሻ
አገልግሎታችንን
በሚልክያ ሚዲያ ሰብስክራይብ በማድረግ የምንለቃቸውን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲከታተሉ በትህትና እንጠይቃለን። ቤተሰብ ሰለሆኑ እናመስግናለን፡፡